ምድርና ሞላዋን በኃይሉ ለገዛው
ሊታይ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ላለው
ለእርሱ እቀኛለሁ አዜማለሁ
1.
እግዚአብሔር ሩህሩህና መሐሪ ነው
ከቁጣ የራቀ ምህረቱ ብዙ ነው
እግዚአብሔር ለሚታገሱት ሁሉ ቸር ነው
ምህረቱም በስራው ሁሉ ላይ ነው
2.
ስለነገሠ ክብር ይገባዋል
ከፍ ከፍ ስላለ ክብር ይገባዋል
ግርማው ስለሚያስፈራ ክብር ይገባዋል
ስሙ ታላቅ ስለሆነ ክብር ይገባዋል
3.
ጉልበት ሁሉ ለእርሱ ይንበረከካሉ
አፍም ሁሉ ለእርሱ በክብሩ ያዜማሉ
መላእክት በሰማይ በክብሩ ያዜማሉ
ቅዱሳን በናፍቆት በምድር ይቀኛሉ