ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #141 / Song #141

ይቅርብኝ ያለም ዝና

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ሀብት ውበትም ይጠፋልና
ላምላክ ክብር እቆማለሁ
እርሱ መርጦኛል እሰራለሁ /2/
1.
በፈርኦን ቤት በክብር ስታይ
ተመችቶኝ ከምንጠራራ
ባምላኬ ቤት ከህዝቡ ጋር
ይሻለኛል መንከራተት ለእርሱ ክብር
2.
ከወርቅ ከንቁ የበልጥብኛል
ካለም ሀብት ሁሉ ይሻለኛል
የርሱን እውነት መሸከሜ
ያኮራኛል በሕይወት ዘመኔ እስከ ፈፃሜ
3.
ሁሉን ነገር እተዋለሁ
ለርሱ ክብር እቆማለሁ
እውነቱን ላለም አውጃለሁ
ማዳኑንም አይቻለሁ መሰክራለሁ
4.
የዓለም ክብር ሁሉ ሞልቶ
ከሚኖረኝ ሁሉ ተስፋፍቶ
ባምላኬ ቤት መጠለሉ
ይበልጣል ለኔ ከዚህ ሁሉ /2/
100%
100%