ሣልወድህ የወደድከኝ
ሳልመርጥህ የመረጥከኝ
በከበረው ደም ገዝተህ
እንዲያው ልጅህ ያረከኝ
አበሳዬን አራቅከው
ቀንበሬን ሰባበርከው
ፍቅርህ ለኔ ልዩ ነው (2)
ስምህን ላሞጋግሰው (2)
1.
ኃጢአተኛ ሳለሁ ጽድቅ የማይገባኝ
መርገሜን ወሰደው ኢየሱስ በደሙ አነጻኝ
የከሰሰኝ ጠላት ከእግሬ ሥር ወደቀ
በረሃው ሕይወቴ ደረቁ ምንጭን አፈለቀ።
2.
ለዚህ የሚያበቃ ጽድቅ እንኳን ሳይኖረኝ
በሰማዩ ስፍራ በቀኙ እንዲሁ አከበረኝ
ምሕረቱ ብዙ ይሄ ታላቅ ጌታ
ከኔ ጋር ሆናችሁ በዜማ አክብሩት በእልልታ
3.
የዕዳ ጽሕፈቴን በደሙ ደምስሶ
ጠላቴን በእጄ ረግጦ ሰጠኝ አሳልፎ
ጽኑ ሥልጣንአለኝ የአምላክ ልጅ ሆኛለሁ
የፈታኝን ጌታ ተፈትቼ አከብረዋለሁ።