ድምፁም ከሰማያት ሰንጥቆ ይወጣል
በአስፈሪ ታላቅ ድምፅ ምድርን ያናውጣል
ሙታንንም ቀስቅሶ ከመቃብር ያወጣል
1.
የእግዚአብሔር ተስፋ ከቶ አይዘገይም
ልጆቹን በእውነት ጌታ አይዘነጋም
በቅርቡ ይመጣል በክብር በዝና በእምነታችን ነቅተን በተስፋው እንጽና
2.
ሁሉም ተመልሶ ኃጢያቱን ቢናዘዝ
ለእግዚአብሔር አምላክ ሰው ሁሉ ቢታዘዝ
አንከርምም በስቃይ በጭንቀትም ሆነን
መጥቶ ያሳርፈናል ጌታ አምላካችን
3.
የምድርን ታሪክ ሁሉ ጌታ ይለውጣል
መርገምን አንስቶ በክብሩ ይሸፍናል
እንደ ወራጅ ውኃ የድል ድምፅ ይሰማል
የድል አድራጊነት እልልታ ይወጣል
4.
የድካም የሰቀቀን ኑሮኣችን ያበቃል
በልጆቹ ልቡ ሁሉ ሀሴትን ያደርጋል
አይናቸውን አንስተው አዳኙን ያያሉ
አምላካችን ነው ብለው ሀሌሉያ ይላሉ