1.
}2xጨለማውም በርሱ ያበራል
ተስፋችንም ይለመልማል
የተዘጋው በር ይከፈታል
2.
ሥጋ ከለበሠው ብዙ ተጠብቋል
የተስፋ ቃል ሁሉ የከንቱ ከንቱ ሆኗል
በሠማይ ወዳለው እናሻቅባለን
ለጥያቄአችንም መልስ እንጠብቃለን
3.
ከሰው የሆነውን አንዳች አንጠብቅም
ከአምላክ ፍቃድ ውጭ የሚሆን አይጠቅምም
በፀሎት በምልጃ እንበረታለን
የማይሰለች ዳኛ በሠማያት አለን
4.
ከልብ ለለመኑት ጌታችን ታማኝ ነው
ቃል ለገባለት ነገር ታምኖ የሚኖረው
ሁሉንም ለማድረግ ጊዜ ይጠብቃል
ባለቀችው ሠዓት በድንቅ ይገለጣል
5.
ጠፊ ለነበርኩት ሕይወትን ከሰጠኝ
በጨለማ ሳለሁ ብርሃን ካበራልኝ
በፊቱ እንዳከብር ካህን ካደረገኝ
የእርሱን በጐነት አውጅልኝ ካለኝ
ለኔ ርስቴ የሱስ ነው /4X/
ለኔስ አላማዬ እርሱን ማስከበሬ
በዚች በምድር ላይ ስሙን ማስጠራቴ
ኑሮ ምለው ይህን ነው/4X/
ከዚህማ ሌላ ሕይወት የሞት ሞት ነው
ከየሱሴ ሌላ ሕይወት ጨለማ ነው
6.
በእርኩሰት ፈንታ መንጻት ከሆነልኝ
በአመፃ ፈንታ ፅድቅን ካለበሰኝ
ከገሀነም ፈንታ ገነት ከተገባኝ
ከባርነት ፈንታ ወራሽ ካደረገኝ
7.
ከቶ ሳላስበው ታዳሚ ሆኛለሁ
የፅድቅን ብድራት ከእጁ አግኝቻለሁ
አልገባኝ እያለ ብዙ ሲያስጨንቀኝ
ለሕይወቴ ምርኩዝ የሱስ ተገኘልኝ