ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #54d / Song #54d

ውለታህ ብዙ አንተ የሠራዊት ጌታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: አ/እ ብርሐነ ወንጌል ሙጥመቃውያን ቤ/ክ መዘምራን
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ስንቱ ተነግሮ ስንቱ ይወራ ጌታ ሆይ
ለእኔ ያረከው እጅግ ብዙ ነው ውለታህ
ከጭንቀት አውጥተህ ሰላምን ሞላኸኝ አብዝተህ
ክብርና ምስጋና ለአንተ ይሁን ለስምህ።
ውለታህ ብዙ አንተ የሠራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔስ ስለ አንተ ውለታ። (2)
2.
ሞትም አፍጦ ሲመጣ በድንገት ወደኔ
ማንስ ነበር ጌታ ካለ አንተ ከጐኔ
ብዙም አትሸበር አለሁኝ ከአንተ ጋር
ብለህ ያወጣኸኝ ከሰይጣን መንጋጋ
3.
መሬት ወደ ወረቀት ቢለወጥ
ባህር በሙሉ ወደ ቀለም ቢቀየር
ክዚያም በኋላ ብጽፍ የአንተን ውለታ
በፍጹም አልችልም ቃላት ያጥሩኛል ጌታ።
4.
ቢጻፍ አያልቅም ጌታ የአንተ ውለታ
ሥራህ ድንቅ ነው አቤት የማትረታ
የእሥራኤል አምላክ ሌቱን የማታንቀላፋ
ልጅህን ጠብቀህ ለክብርህ ያቆምከኝ።
5.
ብርታትና ኃይልን ጸጋንም አብዝተህልኝ
ጉልበት መጠለያ መከታ ጋሻ ሆነኸኝ
ከእሳት አውጥተህ ክብርህን በኔ የገለጽከው
ላውለታህ መልሴ እንደው ተመስገን ብቻ ነው።
100%
100%