ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #145 / Song #145

ካንተ ሚያርቁኝን ሁሉን ነገር ትቼ /2/

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ልከተልህ ጌታ ካንተ ጋራ ሆኜ /2/
በዚህ አለም ያለው አላፊ ነውና
በአንተ ቤት ልኑር ሁሉን ልተውና
1.
ሀብት ዝና ስልጣን መዕረግ
እውቀት ጥበብ ምቾት ድሎት
ካንተ እንዳያርቁኝ
አምላኬ አምላኬ ጠብቀኝ
2.
ራስን መውደድና ለራስ መሯሯርጥ /2/
የሥጋ ምኞትና የአለም ፍላጐት /2/
ካንተ ከፈጣሪ ከቶ እንዳይነጥቁኝ
የሰማይ አባቴ ከለላዬ ሁነኝ
3.
ችግር መከራና ፈተናና ስቃይ /2/
ስደት ረሃብና ጥርጣሬ ፍርሃት /2/
እውነትን እንድሸጥ ከቶ እንዳያደርጉኝ
ከሀዲ ከመሆን አምላኬ ጠብቀኝ
4.
እኔነቴን ክጄ አንተን እንድመስል እኔ
ለውጠኝ ጌታዬ ለክብርህ እንድውል ሁሌ
ይህ የኔ ልመና ምኞቴም ነውና
ሀይልና ብረታትህ ይሁን ከኔ ጋራ
100%
100%