1.
ሕይወት እንደ ጥላ ሲያልፍ
ውበት እንደ ቅጠል ሲረግፍ
ያመኑበት ወዳጅ ሲከዳ
ከኢየሱስ ጋር ሆኜ ልጐዳ
ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል (2)
ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል
2.
አክሊል ከምደፋ በዓለም
የኢየሱስን መስቀል ልሸከም
ሰይጣን ከሚያቆላምጠኝ
ኢየሱሴ በእግሩ ይርገጠኝ
3.
ዙሪያዬን አጅቦኝ ወታደር
በቄሳር ሰገነት ከማደር
ደም እንባ እያፈሰስኩ ለጌታ
ይሻለኛል ለእኔስ ጐልጐታ
4.
በረደኝ አልልም ከንግዲህ
ራበኝ ጠማኝ አልል ከንግዲህ
አፌን በአፈር ውስጥ ቀብሬ
እኖራለሁ ቃሌን አክብሬ
5.
ደግ ሰው ከምድር አለቀ
ጽድቅም ከእግር በታች ወደቀ
አለም ተሞልታለች በክፉ
የሱስን ያዙና እረፉ