የክበር መንፈስ (3)
በአርያም ያለው የእግዚአብሔር መንፈስ
የክብር መንፈስ በእኛ ላይ ይፍሰስ
1.
በእሳት ቁጥቋጦ ውስጥ ሙሴን ያናገርከው
የመላእክትን ምግብ ለሕዝብህ ያደልከው
ስማን ጩኸታችንን እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ
በኢትዮጵያ ምድር የድል መንፈስ አፍስስ።
2.
ሰሎሞን መቅደሱን ሠርቶ እንደ ጨረሰ
በደመና ክብር ከሰማይ ፈሰሰ
ልመናችንን ስማን እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ
እኛን ተናገረን መንፈስህን አፍስስ።
3.
አጋንንቶች ይውጡ ስማቸው ይደምሰስ
ሽባዎች ይነሡ ድውይም ይፈወስ
ጠላት ሲወድቅ እንይ በሰይፍ ሲወጋ
በምድረ ኢትዮጵያ የክብር እጅህን ዘርጋ።
4.
ስምህን እንጠራለን እግዚአብሔር ሆይ መልስ
በጉባኤ መሐል ክብርህ ይመላለስ
ስለ ኢየሱስ ስም ስማን ልመናችንን
በከበረው መንፈስ ጐብኛት ሀገራችንን።