ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #149 / Song #149

የአንድ አባት ልጆች ነን 2X

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የአንድ አባት ልጆች ነን 2X
የአንድ ሀገር ዜጐች ነን 2X
በኢየሱስ ፍቅር ተሳስረን
አንድ ሆነናልና ሁላችን
1.
ከእንግዲህ አይሁድ ግሪክ ማለት
የዘር መከፋፈል ልዩነት
ከመካከላችን አስወግደን
እንኑር በአንድ ሀሣብ ተስማምተን
2.
ባካል ብዙ ብልቶች ቢኖሩም
እጅ እግር ዓይን ተብለው ቢጠሩም
ሁሉም በአንድ ላይ ተገጣጥመው
ይሠራሉ ሙሉ አካል ሆነው
3.
እኛ እርስ በርሳችን ተዋደን
የመለየት መንፈስ ተቃውመን
በፍቅር ብንኖር ሁላችን
የእግዛብሔር አምላክ ልጆች ነን
4.
ፍቅር እግዚአብሔር እራሱ ነው
ለምንኖርበትም ብርሃን ነው
ወንድሙን ሚጠላ ነብስ ይገላል
ክብራን ርቆ በጨለማ ይኖራል
100%
100%