ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #180d / Song #180d

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ማንም የለም ዘለዓለም (2)
1.
ሰው ሁኔታን አይቶ ይከዳል
ጊዜን ጠብቆ ይርቃል
ተስፋ እንደሌለው የማይተው
ጌታዬ እግዚአብሔር ብቻ ነው
ዕውቀትን አይቶ ይከዳል
አላፊ መሆኑን ዘንግቷል
እያየ የአሁን የአሁኑን
ረስቶ አወዳደቄን
2.
ትካዜዬን ለእርሱ ጥዬ
የውስጤን መቃተት ጌታዬ
ሰው እንኳን ቢከዳ ቢጥል
እግዚአብሔር ግን ይረዳል
ሃሳቤን የሚያውቅልኝ
ድካሜን የሚረዳልኝ
የውስጥ ጭንቀቴ የሚገባው
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?
3.
አጽናኝ መስሎ ይጠጋል
ጓደኛ መስሎ ይቀርባል
ጠላትም በእርሱ ተጠቅሞ
ብርሃኔንም አጨልሞ
ግን የሚመካው የምጠጋው
የልቤን የማጫውተው
ድጋፍ መከታ የማደርገው
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?
100%
100%