የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው /2X/
ግሩም ነው እጅግ ግሩም ነው
ማንስ ይችላል ሊያስተውለው /2X/
1.
ይህ አምላካችን ሥራው ታላቅ ነው
ማንም ሥራውን መርምሮ አይዘልቀው
የሚያስደንቅ ነው የእግዚአብሔር ሥራው /2X/
2.
ስግደት ውዳሴ የሚገባው
የፍጥረት ጌታ እሱ ብቻ ነው
እስከዘላለም እናወድሰው /2X/
3.
የሰው ልጆችን ከሞት ያዳነው
እስራታችን የበጣጠሰው
አብ የላከልን ጌታ የሱስ ነው/2X/
4.
ይህንን ጌታ ከፍ እናድርገው
በሰማይ በምድር ሥራው ግሩም ነው
በህይወታችን ከፍ እናድርገው/2X/
5.
እግዚአብሔር አምላክ እኛን የጠራው
ታላቅ ሥራውን እንድናሳይ ነው
አይገባንም ችላ ልንለው/2X/