ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #50d / Song #50d

ልባርከው ጌታዬን ልባርከው

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
ልባርከው ጌታዬን ልባርከው
ልባርከው የሱሴን ልባርከው
በሰማያዊው ስፍራ ባረከኝ
የረገጥኩትን አወረሰኝ
ታዲያ ምኔን ልስጠው ለጌታ
እስኪ ከፍ አድርጉልኝ በእልልታ (2)
1.
የነገረኝን በሙሉ እስከሚያደርግልኝ ታምኖ
በክፉ ቀን መሸሸጊያ በሐሩር ጥላዬ ሆኖ
ሲጠማኝ ምንጭ አፈለቀ ሲርበኝ ደግሞ አጐረሰኝ
ሰው ዓይንህ ላፈር ሲለኝ ኢየሱስ እንዴም ሳይሸሽ
እንደ በደሌ አልከፈለኝ ምሕረቱ ስለኔ በዝቷል
በነፍስና በሥጋዬ በረከቱ ቤቴን ሞልቷል
እንዴት ታዲያ ዝም ልበል ይህንን ሁሉ አይቼ
ልስገድ ልውደቅ በግምባሬ ማደሪያው ቤቱ ገብቼ።
2.
በደሌ በፊቱ በዝቶ ያለቀ የሞትኩ ሲመስለኝ
የጠላቴ ማስፈራራት ጩኸቱ ሲያርበደብደኝ
በዘመርኩበት አንደበት ሙሾ ለማውረድ ስዳዳ
የሞትን ወሬ ሰምቼ ለነፍሴ ሞትን ላረዳ
ስዋከብ ከዚህ ወደዚያ ጭንቀቴን አይቶ ደረሰ
የተዋጋኝን ተዋጋው ዕቅዱን አፈራረሰ
ዛሬማ በኮረብታ ላይ ቆሜ ምስጋና ሰዋለሁ
ሰው ያረገኝን አምላኬን በዜማ እባርካለሁ።
3.
በሰማያዊው በረከት በመንፈስ ባርኮ በረከኝ
በምድር አላጣሁም ይልቁን አትረፈረፈኝ
ሳይሰለች እየተሸከመኝ ቀን በቀን ቤቴን ባረከ
ዓለም የነፈገችኝን ኢየሱስ እጥፍ አረገው
የሱስን ብሎ ወዝ አጣ ያሉኝ ዛሬ ይኸው አፈሩ
ጌታ ሞገሴ መሆኑን በአፋቸው መሰከሩ
ወጥመድ ቢዘጋጅልኝም ኢየሱስ እየቀደመ
ሕይወቴን በረከት ሞላው ደረቅ በትር ለመለመ።
100%
100%