ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #153 / Song #153

ጉዞ ጀምረናል በመርከቡ የሱስ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ጉዞ ጀምረናል በመርከቡ የሱስ
ወደ ፅዮን አገር ከእግዚአብሔር ለመድረስ
ብዙ ፌርማታዎች አሉ ከርሱ ሳንደርስ
እልፍ እንቅፋት አለ ከወደቡ እንዳንደርስ
2x ጉዞ 3x ጀምረናል
1.
ከአንተ ጋር ለመኖር ጌታ ሆይ ናፍቀናል
የሱስ ሆይ ጓግተናል
2.
ግማሹ ሲራገፍ ሌሎች ሲሳፈሩ
የወደደውን ይዞ ይጓዛል ባቡሩ
ከታቀደው ሥፍራ ማን ይሆን የሚደርስ
ተስፋው ጌታ የሆነ የናዝሬቱ የሱስ
3.
እነማን ይሆኑ ወደቡን የሚያዩ
መሰናክሉን አልፈው ከግቡ የሚደርሱ
ይገኙ ይሆን ወይ? ዛሬም እነያሱ
የተስፋዋን ምድር በእምነት የሚወርሱ
100%
100%