ያሻገረኝ በድል ያወጣኝ
ሰባራውን ድልድይ ገጥሞ ያሳለፈኝ
የረዳኝ እግዚያብሔር ነው
ከማንም ቀድሞ ለእኔ የደረሰው (2)
1.
አሳዶቼ ሲማማሉብኝ
ሞቴን ተመኝተው ሲሳለቁብኝ
ቅናቱ ከሰማይ ከመቅደሱ ወጣ
በቁጣው በትር ጠላቶቼን መታ
2.
ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሆነኝ
በጠላቶቼ ፊት ራሴን በዘይት ቀባኝ
በማጽናናቱ ዛሬ ደስ አሰኘኝ
የጠላቶቼንም ሞት በአይኖቼ አሳየኝ
3.
ከእንግዲስ በቃኝ ትካዜ ወድቋላ
ሁሉን በሚችል አምላክ ላይ አርፏል
ለጌታዬ አሁን ወጥቼ እገባለሁ
የሰራልኝንም ታሪክ አወራለሁ