ማን በፊታችን ሊከሰን ይቆማል
ከማለዳ ወገግታም ይልቅ
አምላካችን ያበራል ከሩቅ
1.
የጠላት ጦር ይላገጣል
ጐልያድን መሪው አድርጓል
ልባችንን ሊያቀልጥ ሊያደክመን ይሻል
አምላካችን ግን ለኛ ይዋጋል
2.
በሥጋ ክንድ የታመኑ
ሠረገላ ያሰለፉት
በጦር ብዛት ቢተማመኑም
አምላካችን ግን ከቶ አይተወንም
3.
ያምላክ ቅጥር እንዳይፀና
እነ ጦቢያ ቢነሱና
ቢጣጣሩም ቅጥሩን ለመጣል
አምላካችን ግን ለኛ ይዋጋል
4.
እንደባህርዳር አሸዋ
በፊታችን ቢከማቹም
ከኛ ጋራ ግን ዙሪያችን ያለው
የሚበልጠው ያምላክ ሠራዊት ነው
5.
ሰናክሬም ዛሬም ይፎክራል
ላትድኑ አትልፉ ይላል
ደብዳቤ ይልካል ያስፈራራናል
አምላካችን ግን ለኛ ይዋጋል
6.
የፈርኦን ጦር ጥርሱን ነክሷል
በሠረገሎች ሆኖ ይከንፋል
ዳግም ባሮቹ ሊያደርገን ይሻል
አምላካችን ግን ለኛ ይዋጋል