ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #99 / Song #99

ለዛሬ መድረሴ ይገርመኛል

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 6
ለዛሬ መድረሴ ይገርመኛል
ይህን ቀን ማየቴ ይደንቀኛል
የማይቻል በሙሉ በርሱ ተችሎ
በአሸናፊው ጌታ አምሮ ደምቆ
1.
እንባዬን አበሰ ከአይኔ ላይ
ጌታ አሰበኝ ከሰማይ
እንዴት አችላለሁ ዝም ማለት
ክብሬን ሁሉ ጥዬ ልስገድለት
2.
እስከዚህ ያደረስከኝ እኔ ማን ነኝ
አውቃለሁ እኔማ ደካማ ነኝ
ከአንተ የተነሣ ሰው ሆንኩኝ
በጠላቶቼ ፊት መቼ አፈርኩኝ
3.
ስንቱን አሳለፍከኝ የኔ ጌታ
የጠላቴ ቁጣ ሲበረታ
በዓይኖችህ አይተህ ደረስክና
በመሥጋና ሞላሀኝ እንደገና
4.
ደመናም ባይታይ ነፋስ ባይኖር
ኤልሻዳዩ ጌታ ስሙ ይክበር
ምን ተስኖት ያውቃል ድንቅ ይሠራል
ሰቆቃዬን ሽሮ ያስደስታል
5.
ለዋወጠው ጌታ ታሪኬን
ምን እላለሁ ታዲያ ይመስገን
ምስኪኑን የሚከብር የኔ ጌታ
ስሙ ይክበር ዘውትር ጧት ማታ
100%
100%