ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #11h / Song #11h

አምባችን አምላካችን ነው

A Mighty Fortress is Our God

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
አምባችን አምላካችን ነው
ብርቱ ዕቃ ጦራችን በመከራችን እርሱ ነው
ጽኑ መጠጊያችን
የጥንት ጠላታችን
ሊያጠፋነ ሲሻ
በኃይል በተንኮል ቃል
ጥላቻንም ለብሶ
የሰው ኃይል አይችለውም
2.
በኃይላችን ብንታመን
በቶሎ እንጠፋለን
ግን እግዚአብሔር የመረጠው
እርሱ በኛ በኩል ነው
ስሙንም ብትጠይቅ
የሱስ ክርስቶስ ነው
እግዚአብሔር ጸባአት
የማይለወጠው እርሱ
ነው ድል አድራጊው
3.
ዓለም በሰይጣን ቢሞላም
በጣም ቢያስፈራራንም
እውነት እንደምታሸንፍ
አምላክ ፈቃዱ ሆኗል
ዘመድ ገንዘብ ይቅር
ሟቹ ሕይወት ጭምር
ገላን የሚገድሉ
እውነትህን አይገድሉም
መንግሥትህ ነዋሪ ነው
100%
100%