ከተራራው ላይ እጅ ሳይነካት
ተንከባላ ወርዳ ምስሉን የምትመታ
መንግሥታትን ሁሉ የምትፈጫቸው
ትንሿ ድንጋይ ናት ምድርን የምትማላው
1.
የባቢሎንና የሜዶን ፋርስ
የግሪክና የሮምም መንግሥታት
ይህ ሁሉ አልፈዋል አንድ ነገር ቀርቷል
የምንጠብቀው ድንጋይ በድንገት ይወርዳል
2.
የኤፌሶንና ሠመርኔስ ጴርጋሞን
ትያጥራና ሳርዴስ ፍላዴልፊያም ቢሆን
ይህ ሁሉ አልፈዋል በላዶቂያ ነን
የኢየሱስን መምጫ እንጠብቅ ተጫምተን
3.
ጨረቃ ክዋክብት የምድር መናወጥ
የኢየሩሳሌም መፍረስ የአየር መለወጥ
በተለያዩ ጊዜ ይኸ ሁሉ ሆኗል
የዘመናት ንጉሥ መምጫ ብቻ ቀርቷል
4.
የሕያው የእግዚአብሔር ማኅተም የያዘ
ምፃቱን ጠባቂ ሕዝብ አትሞ ሲጨርስ
ሊቀ ካህናችን ተፈጸመ ይላል
ከመቅደሱ ወጥቶ ሊመጣ ይዘጋጃል
5.
የመጨረሻ ምክር የለገሠልሽ
እባክሽ ላዶቂያ ከእንቅልፍሽ ነቅተሽ
የሚመጠውን ንጉሥ ለመገናኘት
የሰማዩ አምላክ ይደግፍሽ በእውነት