ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #140d / Song #140d

ምስጋና በሰማይ ለሚኖር ለአምላካችን

English Translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ምስጋና በሰማይ ለሚኖር ለአምላካችን
እናቅርብ በአንድነት ሁላችን
ውለታው ብዙ ስለሆነ የኢየሱስ
በዝማሬ ስሙን እንቀድስ
1.
በበረሃ ስለእኛ ተንገላታ በረሃብ
ተጨነቀ አላበው የሰው ልጅ የደም ላብ
ለእኛ ብሎ የሞተልን ጌታ ይባረክ
ፍጥረት ሁሉ ለአዳኙ ጌታ ለሥሙ ይንበርከክ
2.
ሰማይ ሰማያትን ትቶ ለወረደው
የክብር ዙፋን ለሰው ሲል የተወው
ውዳሴ ይገባዋል ጌታችን ይመስገን
በሞቱ የሞትን ሞት ሽሮ ኢየሱስ ነው ያዳነን
3.
መድኃኒት ከሕያው እግዚአብሔር ተሰጠን
አዳኛችን ፈዋሻችን ጌታ ይመስገን
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የእኛ አምላክ
መመኪያና አለኝታ ጌታችን ኢየሱስ ይባረክ
100%
100%