እምነቴን አበርታ ጌታ/2X/
እምነቴን አበርታ የሱስ/2X/
ወጀቡ ሲናወጥ ያኔ እመነቴ እንዳይጠፋ
ማዕበሉ ሲነሳ ደግሞ ትጥቄ እንዳይፈታ
እምነቴን አበርታ ጌታ/2X/
1.
ካንተጋራ ጉዞ የሱስ እጅጉን ይመቻል
በባህር ላይ ደግሞ ስታዝ መራመድ ይቻላል
ግን ፈርቼ ስጠራጠር አልፎም ስመራመር
ባንተ ያለኝ እምነት ጠፍቶ ሰጥሜ እንዳልቀር
2.
በሕይወት ማዕበል ወደብ ምንም ባያቋርጥ
ሁኔታው ሁሉ ቢመስል ተስፋ የሚያስቆርጥ
ማዕበል ሆነ ወደብ ነፋስ የሚታዘዙልህ
እምነቴን አበርታ ልወቅ ከእኔ ጋር እንዳለህ
3.
በዚህ ክፉ ዓለም ስኖር ስወጣና ስወርድ
ስንዴነቴ ቀርቶ ጭራሽ እንዳልሆን እንክርዳድ
የእምነቴ ብርሃን ጠፍቶ ጨለማ እንዳይውጠኝ
ዕለት ዕለት አንተም እኔን አይዞህ ንቃ በለኝ
4.
ሀብትም ቢሆን ክብር ዝና ወይም ብልጽግና
ማጣት መንጣት ውርደት ቢሆን ወይም ጉስቁልና
እየተፈራረቁብኝ ሁሉም በየተራ
ካንተ ተለይቼ እንዳልሄድ ጠብቀኝ አደራ