ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #260d / Song #260d

አምላኬ ሆይ አንተ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
አምላኬ ሆይ አንተ
አንተ ነህ የኔ ለኔ የራራህልኝ
አንተ ነህ ውዴ ለኔ የደረስክልኝ
1.
እኔ በኔ መንገድ እኔው በመረጥኩት
ልጓዝ ስንቀሳቀስ ወደ ሌለህበት
ማንም አልነበረም የሚከታተለኝ
አይጠቅምህም ብሎ ተመለስ የሚለኝ
አንተ ግን ወደኔ ኦሆ መጣህ በፍቅር ቃል
ነፍሴንም ታደካት ከመከራ ስጋት
2.
ዙሪያዬን በሙሉ ሲከንኝ ጨለማ
እኔም ተነሰሁኝ ምንም ሳላቅማማ
ልራመድ በራሴ ወዳላሰብኩበት
ለካስ የምጓዘው ለጥፋት ነበረ
አንተ ስትደርስልኝ መቅበዝበዜ ቀረ።
3.
ነፍሴን የመለስካት ከጥፋት ጎዳና
መልካሙ እረኛዬ አምላኬ ነህና
ምስጋና አለኝ ላንተ ባለውለታዬ
ጣልቃ ገብተ የሆንካት መዳን ለሕይወቴ
አንዳንተ የሚሆን አላየሁምና
እሰዋለሁ ለአንተ ከልቤ ምስጋና።
4.
አጥፊዎችን ሁሉ ፈጥነህ ያጠፋህልኝ
በሞገስ ላይ ሞገስ የደራረብክልኝ
እንዳልቅበዘበዝ ማረፍያ የሆንከኝ
መንገዴ ደልዳላ ሜዳ ያደረክልኝ
ልኡል ሆይ ማደሪያህ ዙፋንህ ይባረክ
ነፍሴን ትገዛለህ ዘላለም ተመለክ።
100%
100%