መልካም ደብዳቤዎች መሆን አለባችሁ
በቃል በተግባር በኑሮአችሁ ሁሉ
ክርሰቲያኖች ለአህዛብ ምሳሌ ሁኑ
1.
ያለነውርና ነቀፋ ሆናችሁ
የህያው አምላክ ፅድቁን ለብሳችሁ
እንደሰማይ ሙሽሮች አምሮ ሕይወታችሁ
ለአህዛብ ይታይ መልካም ሥራችሁ
2.
የምሥራቹን ቃል እየዘራችሁ
በእውነት እውቀት እያደጋችሁ
ለአህዛብ ብርሃን ሁኑ የሕይወት ሽታ
ልታካፍሉ የሰማይን ደስታ
3.
ስለእናንተ መልካም የማያስቡ
በያዛችሁ እምነት የሚቃወሙ
መልካም ሥራችሁን አይተው እንዲያፍሩ
አካሄዳችሁን ካሁኑ አሳምሩ
4.
ለአለም በሙሉ ታማኝ መስካሪዎች
እነዚህ ናቸዉ የእግ/ር ልጆች
ተብላችሁ በእህዛብ ዘንድ በመልካም ሥራ
ስማችሁ እንዲጠራ ብርሃናችሁ ይብራ