ድንጋዩ ተነስቷል መቃብሩም ባዶ ነው
ትንሣኤና ሕይወት ኢየሱስ ተነስቷል
ሞትን አሸንፎ ልጆቹ አድርጐናል
1.
ተነስቷል ጌታችን ሞትን ድል አድርጓል
ከዘላዓለም ሞትም ነፃ አውጥቶናል
መቃብሩን ፈንቅሎ ጌታችን ተነስቷል
ሕያው ነው ዘላዓለም ኢየሱስ ተነስቷል
2.
መቃብሩም ቢታሸግ ሊያስቀራው አልቻለም
የጦረኞች ብዛት ሊያግደው አይችልም
ሕያው ነው ኢየሱስ ሞቶ በዚያ አልቀራም
እግዚአብሔር ይመስገን ሕያው ነው ዘላለም
3.
በማለዳ ሴቶች ተነሥቷል ቢሉንም
አዝነን ወደ አማውስ የሚንሄድ ብንሆንም
ኢየሱስ ተነስቷል በዐይናችን አይተናል
እኛም ምስክር ነን ሞትን ድል አድርጓል
4.
በሽንፈት ተዋጠ ሲእል በዝምታ
በምርኮ የተያዘ በኢየሱስ ተፈታ
የነገሥታት ንጉሱ ኢየሱስ ሕያው ነው
መቃብር አልቻለም ውጦ ሊያስቀረው