ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #52d / Song #52d

ክብር የሆነን ጌታ ሞገስ የሆነን ጌታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጫላ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
ክብር የሆነን ጌታ ሞገስ የሆነን ጌታ
ብቃት የሆነን ጌታ ፀጉድለታችን ፈንታ
ክንዱን በዘመናችን በዓይናችን አይተነዋል
መልካም እረኛ ኢየሱስ እስከዛሬ መርቶናል
1.
በዘመን በዓመታት መሐል የሚገዳደረው የታል
ብቻውን ድንቅን የሠራ የሚኖር እንደ ተፈራ
ለእኛም ይኸው ሞገስ ሆነን
ባሕሩን ከፍሎ አሻገረን
ችግራችንን ረሣነው በየሱስ ስንቱን አለፍነው።
2.
ስንቱን ተሻገርን አለፍን ብምስጋና ሆ እያልን
ስንቱስ ከእግራችን ወደቀ በኢየሱስ እየደቀቀ
ዘመን ሲያልፍ ዘመን ሲተካ ፍሬያችን አብቦ ፈካ
የረገጥነውን ወረስን ዕለት ዕለት አማረብን::
3.
በምድረ በዳ በረሃ የሚያረካ ውኃ ሆን
አልሰለቸን የኛ ጌታ እንደቃሉ ተለመነን
ከመከራ ቀን ሰቀቀን ተማምነን ስሙን ስንጠራ
ደረሰልን በሰዓቱ ኢየሱስ ጌታ፡:
4.
ሸንጐ በኛ ላይ ሲማከር ዲያቢሎስ ሊያጠፋን ሲጥር
ማነው ደርሶ የታደገን በመከራ መርከብ ሆነን
ታሪክ ይናገር ብዙ ነው ብዙ ነው እኛስ ያለፍነው
ከእግራችን ሥር ወድቆ ጠላት ጭንቅላቱን ረገጥነው።
100%
100%