ታላቅ የነገሥታት ንጉስ የሆንከውን ጌታ
ደፋ ቀና ብዬ ዛሬ ልስጥህ ከበሬታ
እንዲሁ ግን በልማድ ስወጣ ስገባ
ድንገት መገለጥ እንዳይሆን አባባ/2X/
1.
ሙላኝ በመንፈስህ ሙላኝ
ንካኝ በመንፈስህ ንካኝ
አንተ ካልነካኸኝ ከንቱ ነው መኖሬ
በደረቀ ህይወት አልደርስም ከሀገሬ
አልገባም ከሀገሬ
2.
ባለብዙ ምህረት ነህ እስካሁን ጠብቀኸኝ
ጀርባህን ሳታዞርብኝ በፍቅር አየኸኝ
ግን አይቀርም አንዴ እኔ ካልተለወጥሁ
ቃልህን ሳላስተውል ወንበር ብቻ ካሞቅሁ/2X/
3.
ቅዱስ መንፈስህን እሻለሁ ደረቅ ህይወት በቃኝ
እስከ ዛሬ ይኸው ስኖር ምንም አልጠቀመኝ
በዘይትህ ሙላኝ እማፀንሃለሁ
የሚያስደስት ፍሬን ያኔ አፈራለሁ--አፈራልሃለሁ
4.
የልቤን መሻቴንና ልመናዬን ሠምተህ
ለውጠኝ እንደምትፈልግ መንፈስህን ሞልተህ
ነቀፋ የሌለኝ ባሪያህ ከሆንኩማ
ቀጥብዬ እገባለሁ ከዚያች ውብ ከተማ/2X/