1.
ፈተና በዛብኝ ማንባቴን አልተውኩም
ወደርሱ ከመጮህ ተስፋ አልቆረጥኩም
አይቀርም አንድ ቁን መልሱን እንደማገኝ
ለጊዜው ጌታዬ የተወኝ ቢመስለኝ።
የእንባዬ ዋጋ የሐዘኔ ሮሮ
አንድ ቀን አይቀርም መመለሱ ቀን ቆጥሮ
2.
ብዙ ነገር ለመንኩ ለኔ የምስማማውን
ከችግር ለመዳን ከመከራም ቢሆን
መልስ አላገኘሁም እኔ እንደፈለኩት
ቀን ልጠብቅ ልትጋ እስካገኝ የሱን ፊት።
3.
የእንባዬን ዋጋ የኔ አምላክ ተምኖ
ይሰጠኛል አንድ ቀን ሁሉን አደላድሎ
እስከዚያ ግን ላዝግም በተስፋ ጐዳና
አንድ ቀን መልስ ማግኘቴ ከቶ አይቀርምና።-