1.
አንድ ችግር በመንገዴ እኔን ሲገጥመኝ
እዚያና እዚህ ስቅበዘበዝ መፍትሔ ላገኝ
ትዝ ትለኝና አንተን አስባለሁ
ዓይኖቼን ወዳንተ አቀናለሁ
ከችግሬም ቶሎ እፈታለሁ።
ዓይኖቼ ወዳንተ ሲቀኑ (3)
ኢየሱስ ቀናልኝ መንገዴ
ብሩህ ሆነ ቀኑ (2)
2.
ትዝ ይለኛል በሕይወቴ መከራ ከቦኝ
ፍርሐት ውጦኝ መውጣት መግባት ጭንቅ ብሎኝ
ኢየሱስ ጌታዬ ጠርቼ ስምህን
ከሁሉ ተርፌ አግኝቻለሁ ራሴን
ተመስገን ጌታዬ ታድገሃል ነፍሴን።
3.
እኔ እስከ ዛሬ የምደርስ መች መሰለኝ
የመትረፍስ ጭላንጭሉን ማን አሳየኝ
ከሁሉም ከሁሉም ያንተ ሥራ በልጦ
አገኘሁ ሁኔታው ባዲስ ተለውጦ
አየሁት ጠላቴን ሲጨነቅ ደንግጦ።
4.
እመካብሃለሁ ጌታ ሁሉን ቻይ ነህ
የሚያስፈራራኝን ሁሉ ትሽራለህ
የጠላት ቀስቱንም ሰብረህ አይቻለሁ
ኤልሻዳይ አምላኬ እታመንሃለሁ
ዘላለም በቤትህ መኖር መርጫለሁ።