1.
እጅግ በረዘመው የኢያሪኮ ቅጥር
ነፍሴ ብትጨነቅ ለሞት ብታጣጥር
አልጠፋም ከልቤ ያለፈው ትዝታ
ዛሬም ድል የአንተነው ነው ቅዱስ የእኔ ጌታ
የሚሳንህ የለም ሁሉን ትችላለህ
ተራራውን ንደህ ባሕሩን ትከፍላለህ
ዮርዳንስም ቆሞ በድል አልፌአለሁ
በኢያሪኮም ላይ ክንድህን አያለሁ
2.
የቃል ኪዳን ታቦት ከፊቴ መቅደሙ
ምልክት ይሆናል ጠላት ለመውደሙ
እኔም እነፋለሁ ቀንደ መለከቴን
ዓለም ሁሉ ያያል አሸናፊነቴን
3.
ዮርዳኖስ ሲከፈል በድል ስንሻገር
አሸናፊነትን ለዓለም ልናገር
ከላይ ያስቀመጥነው መታሰቢያ ድንጋይ
ምስክራችን ነው ጠላታችን እንዲያይ
4.
የኢያሪኮ ቅጥር በእምነት ይፈርሳል
ብሩ ወርቁ ሁሉ ለምርኮ ይሆናል
የጠላትን ሰፈር በእሳት አጋያለሁ
አንተም ስትከብር በገሃድ አያለሁ