ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #170 / Song #170

የታደለ ነው አንተን ይዞ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 5
1.
ሳይባክን ሳይሰለች ጉዞን የጨረሰ
እንዴት ያማረ ነው በጣም የታደለ
ሰው ሆኖ ካምላክ ጋር አብሮ የተጓዘ
ፈቃድህን አክብሮ ቃልህን የታዘዘ
የታደለ ነው አንተን ይዞ /ታዞ/
የሚጨርስ የዓለምን ጉዞ
2.
በአለም ውጣውረድ እምነቱ ታንፆ
ቃልህን ተመርኩዞ በአንተ ስም ተስፋ አርጐ
ለቃል የታዘዘ አንተን የሚጠብቅ
ያም እድለኛ ነው ከሚጠፉት ይልቅ
3.
ሁሉን ይቅር ብሎ አንተን ያከበረ
እኔነቱን ጥሎ ልቡን የሰበረ
እግርህ ሥር ቁጭ ብሎ በቃልህ የረካ
ያም እድለኛ ነው ለደስታ የበቃ
4.
ከአለማዊ ምኞች አራሱን የገዛ
ለሥጋዊ ሥራ ብሎ ያልተገዛ
በቃልህ እረሃብ የሚመላለሰው
ኦ እድለኛ ነው አንተ የመለስከው
5.
ጌታ ሆይ ጉዞዬን ጨርሼ በሰላም
ልምጣ ወደ አንተ ከዚህ ክፉ አለም
እመኛለሁ እና እጄን በእጅህ ያዘኝ
እንደ ተስፋ ቃለህ ጌታ ሆይ አዝልቀኝ
100%
100%