ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #88d / Song #88d

አምላኬ ድንቅ ያረገችው

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: እንድርያስ ሐዋዝ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
አምላኬ ድንቅ ያረገችው
በዝምታ ማዳኑን ያያችሁ
በእልልታ በሆታ ለእርሱ ዘምሩ
አሕዛብ ሁሉ ይስሙት ታምራቱን አውሩ።
1.
በሰዎች ታይታችሁ ስፍራ ያልነበራችሁ
እንደ ምናምንቴ የተቆጠራችሁ
ዛሬ ግን እግዚአብሔር ከትቢያ ያነሣችሁ
ተነሱ አመስግኑት በአንድነት ሆናችሁ።
2.
በምህረት ይቅርታው የተደነቃችሁ
በፍቅሩ ደግፎ የተሸከማችሁ
ኑ በአንድነት ሆነን ስሙን እናክብረው
ጌታ ሰው አርጐናል ምስጋናን እንስጠው።
3.
የጨለማን ዘመን ያሳለፈላችሁ
ለቅሶአችሁን አይቶ ብርሃን ያሳያችሁ
ክብሩን ንገሩለት ለአሕዛብ በሙሉ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ።
4.
ለእኛ ያላረገው ከቶ ምን አለና
አፋችን ዝም አይበል አይከልክል ምስጋና
ምንድን ነው ዝምታው እስኪ ዝም አትበሉ
ሴቶች እልል በሉ ወንዶችም ሆ በሉ።
100%
100%