ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #58d / Song #58d

ኑሮ ያለ ጌታ ታክቶኝ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 6
ኑሮ ያለጌታ ታክቶኝ
ኃጠእቴ አስመርሮኝ
ወደ የሱሴ ብመለስ የእርሱ ደግነት ማርኮኝ
በድል ጎዳና ብገባ ፍቅሩ ነፍሴን ቢገዛ
ግንባሬን ለጠላት ላልሰጥ ቃል ገባሁኝ ለጌታ
በመከራና በጭንቀቴ ሁሉ ጌታን አመልከዋለሁ
ኑሮ ያለእርሱ ጉዳት ነው ከእርሱ ጋር ግን ደስታ
የመልካም ሁኑ መሠረት ይመስገን የኛ ጌታ።
1.
ስንጨነቅ የሚራራ ስናዝን ፈዋሻችን
በበረሃ ዓለም እያለን ስንጠማ አርካታችን
ዞሮ መግቢያችን ኢየሱስ ማረፊያችን አንተ ነህ።
ብንከዳህ አያዋጣንም የደሃ ጎጆአችን ነህ፣
ጌታ ጌታችን ጌታችን አስታውሰን /2/
ብለን ተጣርተን ሣናፍር እስካሁን ተጉዘናል
በነገር ሁሉ መጽናትን ከጌታ ተምረናል፣
2.
የሚያሣፍር ስም አይደለም የስጠኸን ጌታችን
ክርስቲያን ጀግንነት አንደሁ ይረዳልን ልባችን
ክፉውን ሁሉ ተቃውመን ከኃጢአት ጋራ ታግለን
ጉዞችን በድል ያከትማል የጌታን መስቀል ይዘን።
ክብር ክብር ሃሌ ሉያ /2/
የነፍሣት ሁሉ ምስጋና
ዙፋንህን ይክበበው
በቸርነትህ ተደርጎዋል
በልጅህ የዋጀኸው፡፡
100%
100%