በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ
በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ
በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ
በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ
ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ
መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ
1.
በግብጻውያን በደል በዓመጻቸው
ቁጣህ ከላይ ወርዶ ሲፈጃቸው
ደምህ ተቀብቶ በመቃኔ
ምክንያት ሆኖልኛል ለመዳኔ
ተጠነቀክልኝ እንዳልጠፋ
ዙፋንህ ከፍ ይበል ይንሰራፋ
2.
በኮሬብ ተራራ በእሳት አምሳል
ለነብዩ ሙሴ ተገልፀሃል
በእኔም ልብ አንድደህ የፍቅር እሳት
ምስኪኑን ሕይወቴን ስታጋያት
አይቻለሁ እና እንዳቅሜ
አመሰግናለው ይኸው ቆሜ
3.
ከኃጤአቴ በቀር ከመርከሴ
የማውቀው የለኝም ስለራሴ
አንተን ግን አውቃለሁ ስታድንኝ
የድሃ አደግ አባት ስትሆነኝ
በፍቅር ይዘኸኛል በውዴታ
እኔም ላመስግንህ በእልልታ
4.
አጋጣሚ አይደለም ያገናኘን
እንደ አባት እና ልጅ ያቆራኘን
ለእኔ ያሰብከው ያኔ ድሮ
ዛሬ ተፈፀመ ዘመን ቆጥሮ
ያረካህ እንደሆን ይኸው መልሴ
ምስጋና እና ክብር ከውዳሴ