አታላይ ሟርተኞች ኮኮብ ቆጣሪያን
ሊያውቁት አይችሉም ሚስጥርህን
ለኛ ለልጆችህ ያረከውን
1.
ሞራ ገላጭ ጠንቋይ ሟርተኛ
ምንም ነገር አያውቅ መተተኛ
ነገር ግን ሚስጥር የሚገልፀው
ታላቅ አምላክ ያለው በሰማይ ነው
2.
የሚሆነውን ነገር ለልጆቹ
ሰውሮ አያውቅም ለታማኞቹ
በሰማያት ያለው የኛ አምላክ
ሚስጥር የሚገልፀው ጌታ ይባረክ
3.
የኤልያስ አምላክ ከወዴት ነው
የብኤልን ነቢያት ያሳፈረው
ብንጠራው ጌታ አይዘገይም
ረጂያችን እግ/ር አይተወንም
4.
የቅርባችን አምላክ ኃያል ጌታ
ከኛ ጋራ ያለ ነው የማይረታ
የላዶቂያ ወዳጅ አይረሳንም
የሞተልን አምላክ አይተወንም