ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #14d / Song #14d

ከፍ ከፍ አርገን አንተን አክብረን

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ከፍ ከፍ አርገን አንተን አክብረን
ታላቅ ስምህን ደጋግመን ጠርተን
የዝማሬአችን መስዋዕት ወጥቶ
ታሸተዋለህ ልክ እንደ ሽቶ ።
1.
አቤቱ እናመሰግንሐለን (2)
ስምህንም እንጠራላን (2)
2.
የሚሰዋልኝ ለእኔ ምሥጋና
እርሱ ያከብረኛል ብለሃልና
እኛም ወደናል ለማክበር አንተን
ከሁሉም በላይ ክበር ተመስገን።
3.
እንተ ከፍ በል ጠላት ተዋርዶ
እኛም እንስገድ በረከት ወርዶ
ካላንተ ለእኛ ማን አለንና
በሙሉ ኃይላችን ይኸው ምሥጋና።
4.
ከስሞች በላይ ታላቅ ስም ይዘህ
በሰማይ ስፍራ በክብር ያሰህ
እንተ ነህና ለኛ ተስፋችን
ስምህ ሲጠራ ስማን ጌታችን
5.
ብለን ስንጮህ አቤቱ አቤቱ
ፈጥነህ ምትሰማን ኃያል ነህ ብርቱ
ከዘለዓለም እስከ ዘለአለም
በልልታ ሆታ ክበር ተመስገን
100%
100%