1.
ነፍሴ ደስ የምትሰኝብህ ጌታ
በጭንቀቴ የምጠራህ
አጽናኝ ደጋፊ
ብርቱ መከታዬ
ተስፋዬ ሁለንተናዬ
2.
ግሩም ጣፋጭ የሆነው
ቃሉ ኃይልም
በሞት ጥላ ውስጥ
ይዘልቃል
በፊቱ ሁሉንም
ያንበረክካል
የሕይወት ሽታው
ይደርሳል
3.
ከአፉም የጽድቅ
ነገር ይመነጫል
የጸጋን ተክል ያጠጣል
አሕዛብ መዳናቸውን
ያውቁበታል
በፊቱም ደስ ይሰኛሉ
4.
በማዳኑ ሁሉም ይደሰታሉ
መላዕክት ይዘምራሉ
ሠራዊትም ሁሉ ይታዘዙታል
ለዘላለምም ከፍ ይላል