ዝናቡም ጥሎ ይሄዳልና
የዜማ ጊዜያችን ደርሷልና
ስለዚህ በጌታ እንጽናና
1.
በርቱ በርቱ ጌታ ሊጐበኘን ነው
እንባችን ሊታበስልን ነው /2/
2.
የለቅሶ ወራትም ያልፋልና
ሀዘንም በደስታ ይተካልና
ጌታችን ሊመጣ ቀርቧልና
ደስታችን ፍፁም ሊሆን ነውና
3.
ወይናችን ሊያብብ ተቃርቧል
ፍሬያችን ልናጭድ ተዳርሷል
በረከት ህይወታችን ያርሳል
ጠብቀን እኛም እንከብራለን
4.
የጭንቀት የስቃይ ኑሮኣችን
ይነጉዳል ያልፋል ከህይወታችን
ያን ጊዜ ሁሉንም እንረሳለን
በደስታ በፊቱ እንዘምራለን