በእኛ ላይ ታላቅ ምሕረትህ ጥበቃህ ስለ በዛ
ጌታ ሆይ ልንልህ ቻልን ልንጠራህ በምስጋና
ዛሬም እንደገና።
1.
አንተን ታምነን ጉዞ ጀመርን
ተራራ ዳገቱን አለፍን
ልንጨርስ ጥቂት ቀርቶናል
ጌታ ኃይል ያስፈልገናል ብርታትህ ያስፈልገናል።
2.
እንደ ፈቃድህ ባንሆንም
መውደቅ መነሣት ቢበዛም
አልጠፋንም ዛሬም አለን
በእጆችህ ስለ ደገፍከን።(2)
3.
ብንወድቅም እንነሣለን
ብንደክምም እንበረታለን
ጠላት ሐሳብህ አይሠምርም
ጌታ ፍጹም አይተወንም።(2)
4.
እረኛችን ጠባቂያችን
በድል መንገድ እየመራን
ዳገት ቁልቁለቱን አልፈን
ይኸው ለምስጋና በቃን።(2)