ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #26 / Song #26

በትዕግሥት በፀሎት ምፃቱን ተጠባበቅ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
በሀይማኖት ፀንተህ ቁም ከቶ አትነቃነቅ
ዐይንህን ከምድር አንሣ ወደ ላይ ተመልከት
አዳኝህ ሊመጣ ተቃርቧል በእውነት
ልትወርስ ተዘጋጅ የዘላለምን መንግሥት
1.
ዛሬ የምታየውን ለዘላለም አታይም
ጭንቀት መከራ ሀዘን በሰማዩ ቤት የለም
እፎይ ትላለህ በዚያ በሰማዩ እረፍት
እስከዚያ ፀንተህ ቁም በትጋት በእምነት
አዳኝህ ይመጣል ታገሠው በፀሎት
2.
የሥራህን ልታገኝ ዋጋህም ሊከፈል
የዘራኸውን ልታጭድ ወቅቱ እነሆ ደርሷል
ጅማሬህ እጅግ አምሯል ፍፃሜህ ምን ይመስላል
ወዳጄ ካሁኑ መንገድህን ሰልል
ልታገኝ ከአምላክህ ያን ጊዜ የድል አክሊል
3.
ታገሠው ለጥቂት በአይንህ ታያለህ
ሥፍራህን አትልቀቅ አንተም ትከበራለህ
ጠላት እንዳያጠምድህ በሽንገላው አታሎህ
በርታ ፅና በእምነት በያዝከው አላማህ
እስከፍፃሜ ትጋ እንዲያምር ፍፃሜህ
4.
ካለፉት አባቶች ከሀይማኖት አርበኞች
ጌታን በሁሉ አክብረው ከፀኑት ዝነኞች
በአንድ ላይ ሆነን መንግሥቱን እንድንወርስ
ተጠርተናል እንበርታ ሁላችን በክርስቶስ
ተጠርተናል እንበርታ ሁላችን በክርስቶስ
100%
100%