ኦ! ጌታ ሆይ ሥራህ ድንቅ ነው(3)
አደራረግህ ከሰው ልዩ ነው
እጅግ ልዩ ነው ጌታ ሆይ
ከአዕምሮ በላይ ነው።
1.
ሰው በቃ ብሎ የገነዘውን
ድንጋይ አትሞ የቀበረውን
መቃብር ከፍተህ ድንጋይ ፈንቅለህ
መግነዙን ፈተህ በነጻ ለቀህ
በሕይወትህ ታኖራለህ።
2.
አሥራ ሁለት ዓመት ደሜ እጅግ ፈሷል
ሐብቴም ንብረቴም በከንቱ አልቋል
ተስፋ የለህም በቃ ያሉኝ
ጌታን ዳስሼ ፈውስ አገኘሁኝ
ተመስገን አልኩኝ።
3.
ተስፋ ተቆርጦ ምን ይሁን ሲባል
እምነት ሲጠፉ ጉልበትም ሲዝል
በተዘጋው በር በድንገት ገብተህ
በሚያበራ ልብ በክብር ተገልጠህ
ታሳርፋለህ።
4.
ስንቶች እያሉ የተከበሩ
በ ዕውቀት ያጌጡ በወርቅ በብሩ
አንደ እኔ ያለ ደካማ ወደህ
ብርቱን አሳፈርክ ስምህን አክብረህ
አንተ ድንቅ ነህ።