ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #142d / Song #142d

እሰይ በሰማይ ቤት አለኝ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ስብሐት ለአምላክ፣ 1975
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
እሰይ በሰማይ ቤት አለኝ
እሰይ በሰማይ ቤት አለኝ
እሰይ በሰማይ ቤት አለኝ
በየሱስ ክርስቶስ ከታመንኩኝ
1.
ኃጢአቴን ሁሉ አጥፍቶልኛል
የሰማይ ቤቴን ሊያወርሰኝ።
2.
ባለ ኮከብ ዘውድ. በሰማይ ቤት አለኝ
በየሱስ ክርስቶስ ከታመንኩኝ።
3.
የአምላኬን ፊት አየዋለሁኝ
በየሱስ ክርስቶስ ከታመንኩኝ።
4.
ከመላእክት ጋር እዘምራለሁኝ
በሰማይ ቤቱ ከቅድሳን ጋር።
5.
በልተሰማ ዜማ ክብሩን እንገልጻለን
በሰማይ ቤት ከቅዱሳን ጋር።
100%
100%