ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #134d / Song #134d

ናፍቆቴ እጅግ በዝቷልና

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ደረጀ ከበደ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ናፍቆቴ እጅግ በዝቷልና
ኢየሱስ እባክህ ቶሎ ና (4)
ኢየሱስ ቶሎና
ናፍቆቴ በዝቷልና
1.
ዘወትር የተስፋ ሰው መሆን ይበቃኛል
ሰዓቱ ነው አሁን ላይህ ይገባኛል
ኢየሱስ ቶሎ ና
እንደ ውኃ ጠማኝ ዓይንህን መመልከት
ቶሎ ብትመጣልኝ አሁን ምን አለበት
እባክህ ቶሎ ና።
2.
ዓይኖቼን ወደ ላይ ማንጋጠጥ ከጀመርኩ
ቀናቶች አለፉ ዘመናትን ቆጠርኩ
ኢየሱስ ቶሎና
እንድጠብቅህም ዓይኔ በእንባ ሞልቶ
ናፍቆት አሸነፈኝ መሯሯጡ በዝቶ
እባክህ ቶሎ ና።
3.
አንተን የማያውቁ የት አለ ጌታ አሉ
ስለነሱ ሳይሆን ስለኔ ግን ናልኝ
ኢየሱስ ቶሎ ና
እምነትና ተስፋ ጌታ መተኪያቸው
በሚጸና ፍቅርህ አንተ ለውጣቸው
እባክህ ቶሎ ና።
100%
100%