የቀድሞ ባርነት ከእንግዲህ ይበቃል
ከእንግድነት ሀገር ጠርቶናል አምላካችን
እንታጠቅ ወገኖች ልንሄድ ወደ ሀገራችን
1.
እኛ ግን ሀገራችን በላይ በሰማይ ናት
ለዘላለም አርፈን ሁሌ የምንኖርባት
መሪያችን ኢየሱስ ነው ወደፅዮኑ አለት
ወደዚያ እንገስግስ ወደ ዘላለም ህይወት /2/
2.
በዚህ በዲያብሎስ ግዛት በፍፁም አንኖርም
በማይዘልቀው ዓለም ወደፊት አንገፋም
ሀዘንና ጭንቀት ሞት በማይገኝበት
ሥፍራ ተዘጋጅቶልናል ዘላለም ምናርፍበት
3.
በዚህ በጠፊው አገር ምን ህብረት አለን
ሀብቷና ውበቷ በፍፁም አይማርከን
ጥበብና እውቀቷ እኛን አያታለን
ወገባችን እንታጠቅ ልንገባ አገራችን
አምሮና ቆንጅቶ ተውቧል ቤታችን
ሽታው ከሩቅ ያስደስታል ከተማችን
መራብና መራቆት ማዘንና መጨነቅ
መልፋትና መድከም ማፈርና መናቅ
በዚህ በጠፊው ዓለም አብረው ሊጠፋ ነው
የዚህ ዓለም ጣጣው እነሆ መረሣቱ ነው
በሉ ተዘጋጁ ስንቃችሁን ሰንቁ
ካላችሁበት ሥፍራ ቶሎ በሉ ንቁ
የእንግድነት ሀገር ታሪኩን ሁሉ አብቁ
ወደ አገራችን ልንጓዝ ጊዜው መሆኑን እወቁ
4.
በዚህ በአላፊው አለም ለምን እንኮራለን
የኔ ነው እያልን እንዴት እንገፋለን
ትላንትም የታየው ዛሬ በሚጠፋው ምድር
ምን አንድነት አለን ሁሉም ነገር ይቅር
5.
የፃድቃን እልልታ የቅዱሳን ምስጋና
በሰማይ ሰማያት ለሆነው ገናና
ይገባዋል እያሉ መላዕክት በሚያዜሙበት
ለእኛም አገር አለን ጠላት በማይደርስበት