ተመስገን ጌታዬ ክብር ገናንነት ለስምህ ይሁን
ተመስገን የሱስ ሆይ ክብር ገናንነት ለስምህ ይሁን
1.
በትጋት እንድቆይ ሳይደክም ጉልበቴ
ኃይልህን አስታጥቀኝ ከላይ መድኃኒቴ
በብዙ ውዥንብር ቢያጥለቀልቅ ጐርፉ
ጠላቶች በአንተ ስም ሁሉም ተሸነፉ።
2.
የኑሮዬ ተገን ክብሬ መከታዬ
ኃይሌም ይታደሣል አንተ ነህ ተድላዬ
ማዕበሉ ተነሥቶ ሊያሰጥመኝ ሲቃጣ
በገሃድ አያለሁ ረዳቴ ስትመጣ።
3.
የእግዚአብሔር ቸርነት አያልቅም ቢቆጠር
ነነዌም ብትሠራ ኃጢአት በማዘውተር
አምላክም አስቦ እነርሱን ለመምከር
አዘዘው ዮናስን ለሕዝቡ እንዲናገር።