ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #44d / Song #44d

ምስጋናዬ ይኸው ለአንተ ጌታ (3)

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ኅብረት ቃለሕይወት ቤ/ክ «ሀ» መዘምራን
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
ምስጋናዬ ይኸው ለአንተ ጌታ (3)
አክብሮቴን ልስጥህ ስለ ውለታህ (3)
ድንቅ በሆነው እጅህ ዳሰኸኛል
ፈውሰህ ሙሉ ሰው አርገኸኛል
ኦ! ምስጋናዬ ዝማሬዬ ለጌታዬ(2)
1.
ከሽባነት ወጣሁኝ የሱስ በእጆቹ ዳሶኝ
ተፈውሼ እዘላለሁ ለአምላኬ ዘምራለሁ
መች ወዶት ሽባነቴን ፈውሷል ሰውነቴን
ውለታው በዝቶብኛል ላከብረው ይገባኛል።
2.
ጐባጣው ሰውነቴን ዳሰሰው አካላቴን
ጸንቼ መቆም ቻልኩኝ አምላኬን አክብሩልኝ
እጆቹ ድንቅ ናቸው በምድር አቻ የላቸው
ደጋግፎ አቁሞኛል ምን ልስጠው ቸግርኛል።
3.
የዓይኔ ብርሃን ጠፍቶ ማን አዘነልኝ ከቶ
ጌታ ግን ጠጋ አለኝ ፈውሴን አበሰረልኝ
መች ጨከነ ኢየሱስ መጣ እንጂ ዓይኔን ሊያብስ
ወደድኩት ይህን ጌታ ምስጋናዬን በእልልታ።
4.
አንድ ልጅ ሞቶብኝ ላልተካው መበለት ነኝ:
ለመቅበር ስሄድ ሳለሁ ከኢየሱስ ተገናኘሁ
አዝኖልኝ ቀረበና ቃሬዛውን ነካው
ልጄን ከሞት አስነሣው ፈወሰው ምኔን ልስጠው።
100%
100%