1.
ዓላማ ይዞ የተሰለፈ የሚያስፈራ የአንተ ሰራዊት
ጠላትን ሁሉ እያሸነፈ በአንተ መሪነት ቀንና ሌሊት
ባሕር ተሻግሮ በምድረበዳ ጊንጡን ረጋግጦ
ጥቂቱ ሕዝብህ ከአንተ ጋር በዝቶ ርስቱን ጨበጠ ከብዙ በልጦ
ሕዝብን አበዛህ (2)
የአገሪቱንም ወሰን አሰፋህ
የማዳን እጅህን ለእኛ ዘረጋህ (2)
2.
የሰናፍጯን ቅንጣት ቢዘራ ጌታ በምድር እንድትበዛ
ያ ጉልበተኛ መጥቶ ረገጣት እንዳትበቅል መስላው ፈዛዛ
ግን አልተሳካም አምልጣ ወጣች ሄደች አደገች
ጌታ ይመስገን ድንበሯ ሰፋ ለደካከሙት መጠለያ ሆነች
3.
ኦ ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ እያሸነፈ ዘለዓለም ነዋሪ
እንደ አምላካችን ያለ ታዳጊ ከቶ የት አለ ተወዳዳሪ
ጩኸትን ሰምቶ ምስኪን ድሆችን ዘይት የሚቀባ
በአደባባዩ በቤቱ ተክሎ የሚያለመልም እንደ ዘንባባ