ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #42d / Song #42d

ምስጋና ይገባሃል የሠራዊት ጌታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ምስጋና ይገባሃል የሠራዊት ጌታ
ከቶ ማን ተገኝቷል ማኅተሙን ሊፈታ
ምስጋና ይገባሃል ክብርም ይገባሃል
መወደስ ይገባሃል መንገሥም ይገባሃል
1.
የመጀመሪያውና የመጨረሻው
ክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሚመጣው
የእግዚአብሔር በግ የታረድከው
በደምህ ዕድፈቴን ያጠብከው።
2.
እሥራታችንን የበጣጠስከው
ቀንበራችንን ደግሞ የሰበርከው
አርነታችንን በደምህ ያወጅከው
በላይ በአባትህ ቀኝ ያለኸው።
3.
ዋጋችንን ልትሰጠን ልታሳርፈን
በማይነገር ሐሴት ልታስደስተን
በጽዮን ውስጥ እፎይ ልታሰኘን
የምትመጣው እኛን ልታጽናናን።
100%
100%