ነገር ግን ሞተሃል ሥራህን ዘንግተህ
ስለዚህም ንቃ ተው ንስሀ ግባ
ሳታስብ መጣለሁ ልክ እንደሌባ
1.
ተግባርህን ትተህ ከዓለም ተባብረህ
እስከመቼ ድረስ ትኖራለህ አብረህ
ተው ተመለስ ልጄ ሁሉን ነገር ትተህ
ለዘላለም እንድትኖር ከእኔ ጋር ሆነህ
2.
በራድ ወይም ትኩስ አልሆንክም ወንድሜ
ከአፌ እንዳልተፋህ ልንገርህ ደግሜ
ሀብታም ነኝ አትበል ሁሉን ነገር አጥተህ
የእኔንም መንፈስ ፀጋ አልባ ሆነህ
3.
ሀብታም እንድትሆን እንዲሁም ባለፀጋ
በፀናው እምነትህ ቅረብ ኢየሱስ ጋ
ሀፍረት ለመሸፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ
ለሥጋ አትታዛዝ ህይወትህን ቀድስ
4.
እኔ እልሃለሁ ሥራህን አውቃለሁ
የተከፈተ በር ከፊትህ አድርጌአለሁ
ማንም ሰው ሊዘጋው ከቶ የማይችለው
አንተ ብቻ ፅና ትዕዛዜን ጠብቀው