ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #168d / Song #168d

ኑሮዬ ከአንተ ጋራ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ኑሮዬ ከአንተ ጋራ
ሸለቆ ቢሆን ተራራ
የደስታ ቢሆን የዕንባ
ትሻለኛለህ አባባ
1.
ላያጠግብ ኩርማን እንጀራ
ቀንና ሌሊት ብሰራ
አለቀ ኃይሌ ጉልበቴ
በክንድህ ይሁን ዕረፍቴ
የቀረው ጥቂት ዘመኔ
በአንተ ቤት ልረፍ መድህኔ (2x)
2.
ከዛሬ ነገ ይሻል ብዬ
ብዙ ሮጥኩኝ ጨርቄን ጥዬ
በዓለም ያየሁት አበሳ
እስከ መቼም አይረሳ
ከእንግዲህ በቃ ሩጫዬ
መስቀልህ ሆኗል ምርጫዬ (2x)
3.
ክፉ ዓለም ክብር የጐደላት
ጦር እንጂ ሰላም የሌላት
ሰው በአምላክ አምሳል ተፈጥሮ
ወደ አውሬነት ተቀይሮ
እርስ በርስ ስታብላላ
በውሸት ዕውቀት አታላ (2x)
4.
የዚህ ዓለም ጌታ ከመሆን
ሰማይን ምድርን ከመግዛት
እራስን ላንተ አስገዝቶ
ድሃ ተብሎ መጠራት
ክብር እንደሆነ አወቅሁ ጠንቅቄ (2x)
በቤትህ ልኑር ማቅቄ
100%
100%