1.
ቀድሞ ያልነበረን ማኖር ነው ወይ
ነዋሪ የሚመስለንን ማጥፋት ነው ወይ
ከፍጡር አዕምሮ በላይ ነው
ከእርሱ የሚወዳደር የቱ ነው
ለእግዚአብሔር የሚሣን አለ ወይ (2)
ቀድሞም አልነበረም
ዛሬም ቢሆን የለም
አይኖርም ዘለዓለም
2.
ተራራውን ሜዳ ማድረግ ነው ወይ
ባሕር ውቅያኖስን ማድረቅ ነው ወይ
ኧረ እስቲ የቱ ነው የማይችለው
በእውነት አምላካችን ታላቅ ነው
3.
እንኳንስ በዓለም የትም የሌለ
መድህን ለበሽተኞች ሥሙ አለ
ይህ ተአምረኛ ስም ሲጠራ
ሰይጣናት ሲበኑ እንደ አቧራ
4.
ጠላታችን ሰይጣን ሊያጠፋን
የዘለዓለምን ሞት ሊያወርሰን
ግን ቸሩ አምላካችን ራራልን
ሞታችንን ሞቶ አዳነን